ኮሌጁ በጠንካራ የሥራ አፈጻጸም ተሸላሚ ሆነ
Posted 2021-02-05 07:46:53
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ከጥቅምት 11እስከ ጥቅምት 12/2013 በባህርዳር ከተማ ባዘጋጀው መድረክ የዘርፉን የ2013 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ የ2013 በጀት ዓመቱን የቀሪ 9 ወራት የዕቅድ ትውውቅ አድርጓል፡፡ በሥራ አፈጻጸም ግምገማና በእቅድ ትውውቅ መድረኩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አመራሮች፤ የዞን ቴክኒክና ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ክልሉ በሥሩ የሚገኙ 120 ኮሌጆና ፖሊቴክኒክ ኮሌጆችን በማወዳደር የላቀ አፈጻጸም ላሳዩት የእውቅና ሰርትፍኬት ከመስጠት በተጨማሪ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተርና የላፕቶፕ ቁሳቁስ ሽልማቶችን ሰጥቷል፡፡ የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በነበረው የላቀ አፈጻጸም 3ኛ ደረጃ በመውጣቱ የሰርትፍኬትና የፕሪንተር ማሽን ተሸላሚ ሆኗል፡፡