የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ

Posted 2022-08-02 12:46:41
News image

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ -------------------------------------------------------------------------- የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት የእቅድ ትግበራ ትውውቅ መድረክ በኮሌጁ ቤተመጻሕፍት አካሄዱ። የኮሌጁ የእቅድና በጀት ዝግጅት ባለሙያ አቶ ሰለሞን በልሁ የኮሌጁን የ2014 እቅድ አፈፃፀም ከቁልፍና ከአበይት ተግባራት አንፃር በመከፋፈል ዝርዝር ሪፖርቱን አቅርበዋል። የበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸም ረፖርት ከቀረበ በኋላ የቀጣይ 2015 ዓ.ም. የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ ትውውቅ የተደረገ ሲሆን የእቅድ ትውውቅ መድረኩን የኮሌጁ ዲን አቶ መላኩ አራጋው መርተውታል። በእቅድ ትውውቁ በዝግጅት ምእራፍ በመጀመሪያው የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ ወቅት በሚከናወኑ የርብርብ ተግባራት ላይ በኮሌጁ ዲን ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ቀርቧል። በመድረኩ የቀረበውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ በጀት ዓመት የመጀመሪያው 90 ቀናት እቅድ ትውውቅ አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከመድረኩ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም የመልካም አስተዳደር ጥናት ሪፖርት ቀርቧል። ኮሌጁ ከሦስት ወራት በፊት የ9 ወራቱን ሪፖርት በገመገመበት ወቅት በኮሌጁ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ ተብሎ ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተነሳና ይህንኑ አስመልክቶ ጉዳዩን የሚያጣራና በጥናት የሚያቀርብ አምስት አባላትን ያቀፈ የመልካም አስተዳደር ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጥናት ውጤት በኮሚቴው ሰብሳቢ በአቶ አብዱሻኪር ሰይድ ለመድረኩ ቀርቧል። "ምንም ይሁን ምን ማንኛውም የመልካም አስተዳደር ችግር የሚመነጨው ከመልካም አስተዳደር መርሆዎች ጥሰት ነው" ሲሉ የኮሚቴው ሰብሳቢና የሪፖርቱ አቅራቢ አቶ አብዱሻኪር ሰይድ ተናግረዋል። የመልካም አስተዳደር ችግር ሲባል ምን ማለት ነው? በኮሌጃችን የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምን አይነት ናቸው? በኮሌጁ አሉ የተባሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችስ ምንጫቸው ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ አጥኚ ኮሚቴው የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በመዳሰስ የጥናቱ መነሻ አድርጓል። በጥናቱ መሰረት በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተጠቀሱ ሲሆን ለችግሮቹ መፈጠርም ባለቤት ተሰጥቷቸዋል። የችግሮቹን ምንጮችና ችግሮቹ የተስተዋሉባቸውን የሥራ ክፍሎች በመለየትም በቀጣይ የእርምት እርምጃ ለመውሰድና ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚያመች መልኩ የመፍተሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።


News

News image
2022-08-17 17:21:05
በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሪፎርም አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ
News image
2022-08-02 12:52:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ
News image
2022-08-02 12:46:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
Kombolcha Polytechnic College