የኮሌጁ ኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ የዓለም ባንክ ፕሮጀክት አፈጻጸም ያለበትን ሂደት ገመገመ
Posted 2021-02-05 07:50:05
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን በአገር አቀፍና በምስራቅ አፍሪካ የልዕቀት ማዕከል ለማድረግ አመራሩ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን አዘጋጅቶ በማቅረብና ከሌሎች አቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፉ ኮሌጁን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ፕሮጀከቶች ውስጥ ኮሌጁን በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ከዓለም ባንክ በተገኘ የ12.85 ሚሊዮን ዶላር በርካታ ተግባራትን ለማከናወን የተያዘው ፕሮጀክት ዋናው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴና ተግባራዊነት የሚከታተል የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ ቀደም ሲል የተቋቋመ ሲሆን ቦርዱ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለበትን ሂደት በደሴ ከተማ ሚልቦርን ሆቴል ከኮሌጁ የክላስተር ኮሌጆችና አጋር ኮሌጆች ጋር በመሆን ግምገማ አካሂዷል፡፡