በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ያለንክኪ የሚሠራ የእጅ መታጠቢያ ቴክኖሎጂ ተተገበረ
Posted 2021-02-05 07:56:48
የኮሮና ቫይረስን እንዴት እከላከላለሁ? የኮሮና ቫይረስ መከላከያ እርምጃዎች:- አዘውትረን እጆቻችንን በውኃና በሳሙና ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች ያህል በሚገባበ ማሸትና ማፅዳት ፤ -ሲያስለንና ሲያስነጥሰን በሶፍት ወይም ክርናችንን በማጠፍ አፍና አፍንጫችንን መሸፈን ፤ አክታን በየቦተው አለመትፋት-ዐይንን አፍንጫንና አፍን ከመነካካት መቆጠብ ፤ ህዝብ በተሠበሠበበት አካባቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማሰከ (ጭንብል) መጠቀም-በኮሮና ቫይረስ ከተያዘም ሆነ ከታመመ ሰው ጋር በአካል የቀረበ ግንኙነት አለማድረግ ፤ አዘውትረን የምንጠቀምባቸውን የጋራ መገልገያ ቁሳቁሶች በአልኮል ወይም በሳኒታይዘር ማፅዳት የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች የተለመዱ ምልክቶች:- ትኩሳት ፤ ደረቅ ሳል ፤ የድካም ስሜት ያልተለመዱ ምልክቶች : - የቁርጥማትና የማሳከክ ስሜት ፤ የጉሮሮ ቁስለት ፤ ተቅማጥ ፤ የዐይን እብጠት ፤ የራስ ምታት ፤ የመቅመስ ወይም የማሽተት ስሜትን ማጣት ከባድ ምልክቶች : - ለመተንፈስ መቸገር ወይም የትንፋሽ ማጠር ፤ የሚያሰቃይ የደረት ህመም ፤ የመናገር ኃይል ማጣትና እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻል