የኮሌጁ ሠራተኞችና ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ስነስርአት አከበሩ

Posted 2021-03-17 03:40:23
News image

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ለ45ኛ በአዓም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ112ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) "የሴቶችን ሁለንትናዊ መብት የሚያከብር ትውልድ እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የካቲት 29/2013 በኮሌጁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ስነስርዐት ተከብሯል፡፡ በአሉን አስመልክተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የውስጥ ኦዲት ባለሙያ ወ/ሮ ጌጤ ክብረት እንደተናገሩት ሴቶች በየትኛውም መስክ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም የመሪነት ቦታዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም ሴቶች አይችሉም የሚለው ስር የሰደደ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ውጤት ያመጣው በመሆኑ ሴቶች ሊታገሉት ይገባል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ጌጤ አያይዘው እንደተናገሩት ሴቶች እድል እንጅ ችሎታ አላጡም ብለዋል፡፡ ክብረ በአሉን ደማቅ ለማድረግ አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ልዩልዩ ስነ ግጥሞች በየፕሮግራሙ መሀል መሀል በሰልጣኞች ቀርቧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በቴክኒክና ሙያው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ ደረጃ በመዳሰስ ለመወያያ የሚሆን አጠር ያለ ፅሑፍ በአቶ ነገሰ ከበደ የቀረበ ሲሆን የትምህርት መብትን በሶስት ዋናዋና ክፍሎች ማለትም የመማር መብት፤ የትምህርት ተደራሽነት መብትና በትምህረት ቤት ውስጥ ሴቶችንም ወንዶችንም እኩል የትምህርት ተደራሽነት እንዲኖራቸው ማድረግ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም በቴክኒክና ሙያ ትምህርታቸውን ተምረው ውጤታማ የሆኑ ሴት አሰልጣኞች ተሞክሯቸውን ለመድረኩ ታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡ **በህዝብ ግንኙነት የሥራ ሒደት የተዘጋጀ **

የኮሌጁ ሠራተኞችና ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ስነስርአት አከበሩ

News

News image
2022-08-17 17:21:05
በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሪፎርም አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ
News image
2022-08-02 12:52:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ
News image
2022-08-02 12:46:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
Kombolcha Polytechnic College