ኮሌጁ በሰባተኛው ክልል አቀፍ የቴክኖሎጂ፤ የካይዘንና የክህሎት ውድድር ሽልማቶችን ተረክቦ ተመለሰ

Posted 2021-04-15 04:45:58
News image

ሰባተኛው ክልል አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ሲምፖዝየም፤ ኤግዝቢሽን፤ የካይዘንና የክህሎት ውድድር ከሚያዝያ 2 እስከ ሚያዝያ 5/2013 በደሴ ከተማ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተካሄደ፡፡ በውድድሩ በርካ የክልሉ ኮሌጆችና ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በቴክኖሎጂ፤ በካይዘን፤ በክህሎትና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ያካሄዱ ሲሆን የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና ሰልጣኞች በቴክኖሎጂ፤ በካይዘን፤ በክህሎትና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ጠንካራ ፉክክር በማድረግ 14 ሽልማቶችንና 2 ዋንጫዎችን ከአብክመ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ከሆኑት አቶ ድረሴ እሸቱና ከአቶ ካሳ ዓለሙ እጅ ተረክበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሌጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማቴሪያልና በሰው ኃይል አደረጃጀቱ አቅሙን እያሳደገ እና የሚሰጠውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከዓለም አቀፍ ገበያው አንፃር ተወዳዳሪ ለማድረግ የካይዘን የጥራት ማስጠበቂያ መሣሪያ የሆነውን የካይዘን ፍልስፍና ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ እያደረገ በመምጣቱ ለውድድር ቀርቦ አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ኮሌጁ በካይዘን የጥራት ስራ አመራር ትግበራ ብልጫ ማግኘቱ በአማራ ክልል የቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ለመሆን የሚያስችለውን ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን አመላካች ነው፡፡ **በህዝብ ግንኙነት የሥራ ሒደት የተዘጋጀ **

ኮሌጁ በሰባተኛው ክልል አቀፍ የቴክኖሎጂ፤ የካይዘንና የክህሎት ውድድር ሽልማቶችን ተረክቦ ተመለሰ

News

News image
2022-08-17 17:21:05
በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሪፎርም አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ
News image
2022-08-02 12:52:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ
News image
2022-08-02 12:46:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
Kombolcha Polytechnic College