የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር ለኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመኪና ድጋፍ አደረገ

Posted 2021-06-26 05:16:31
News image

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በአገር አቀፍና በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ከዓለም ባንክ ባገኘው 12.85 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በኢስትሪፕ (EASTRIP) ፕሮጀክት በእቅድ ተይዘው እየተፈፀሙ ካሉት ተግባራት መካከል የተሸከርካሪ ግዥ ጥያቄው በብሔራዊ ኢስትሪፕ ማስተባበሪያ ዩኒት በኩል ተፈፅሟል፤፤ በብሔራዊ ማስተባበሪያ ዩኒቱ በኩል በመጀመሪያ ዙር ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡት 23 ፒክ አፕ ተሸከርካሪዎች ውስጥ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር ድልድል መሰረት አንድ ፒክ አፕ ለኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመሰጠቱ በኮሌጁ ንብረት ኦፊሰር በአቶ ረታ ይማም በኩል ኮሌጁ ተሸከርካሪዋን ተርክቧል፤፤ ተሸከርካሪው በኮሌጁ እየተተገበረ ለሚገኘው ኢስትሪፕ ፕሮጀክት ሥራ አገልግሎት እንዲውል ታስቦ የተገዛ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር የመኪናዎእ ርክክብ እንዲፈፀም ከጻፈው ደብዳቤ መረዳት ተችሏል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር ለኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመኪና ድጋፍ አደረገ

News

News image
2022-08-17 17:21:05
በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሪፎርም አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ
News image
2022-08-02 12:52:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ
News image
2022-08-02 12:46:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
Kombolcha Polytechnic College