በሥራና ክህሎት ስልጠና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የጀርመን ልማት ባንክ (KFW) ለኮሌጁ የስልጠና ቁሳቁሶች ዲጋፍ አደረገ

Posted 2022-03-24 12:40:03
News image

በአሸባሪው የህወኃት ቡድን ወረራና ዝርፊያ የተፈጸመበትን የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መልሶ ለማቋቋም በፌዴራል መንግስት የሥራና ክህሎት ስልጠና አስተባባሪነት የጀርመን ልማት ባንክ (KFW) ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የማሰልጠኛ ቁሳቁስ ለኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲጋፍ አደረገ፡፡ የማሰልጠኛ ቁሳቁሶቹ ለግብርና፤ ለውኃና ለቴክስታይል ጋርመንት የስልጠና ዘርፎች ዲጋፍ የሚውሉ መሆኑን ድጋፉን በጀርመን መንግስት ስም ለኮሌጁ ያስረከቡት ዶክተር ሮበርት ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ስልጠና ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በአሸባሪው ቡድን ዘረፋ ከመፈጸሙ በፊት የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሁለንትናዊ አደረጃጀቱ ከክልል አልፎ በአገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ኮሌጅ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው ኮሌጁን መልሶ ለማቋቋም የፌዴራልና የክልሉ መንግስት በትኩረተረ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ ክብርት ሚንስተሯ አክለው እንደተናገሩት የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) ለመሆን በዓለም ባንክ የገንዘብ ዲጋፍ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘውን የምስራቅ አፈሪካ ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክትን (East Africa Skills for Transformation and Regional Integration Projeket- EASTRIP) በመተግበር ላይ ያለ ኮሌጅ በመሆኑ ለዚህ ስኬቱ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

በሥራና ክህሎት ስልጠና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የጀርመን ልማት ባንክ (KFW) ለኮሌጁ የስልጠና ቁሳቁሶች ዲጋፍ አደረገ

News

News image
2022-08-17 17:21:05
በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሪፎርም አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ጀመረ
News image
2022-08-02 12:52:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ
News image
2022-08-02 12:46:41
የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2014 እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ
Kombolcha Polytechnic College